Sunday, September 22, 2024
spot_img

ፍርድ ቤት ፌዴራል ፖሊስ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን እነሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤን ይዞ እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የፀረ ሽብርና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት በእነሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ መዝገብ የተሰከሰሱ ግለሰቦችን ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ጋር በመተባበር ይዞ እንዲያቀርባቸው ትእዘዝ ሰጥቷል።

ሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ፣ ብርጋዴሬ ጀነራል ምግባረ ኃይሌ እና ብርጋዴር ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ 74 የጦር መኮንኖች የነበሩ ግለሰቦች ናቸው ክስ የተመሰረተባቸው።

አቃቤ ህግ ሁሉም ተከሳሾች የህወሓት የሽብር ቡድንን ተልእኮ በመቀበል ህገ ወጥ ወታደራዊ ቡድን በማቋቋም የሰሜን እዝንና የፌዴራል ፖሊስን ብሎም በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በሚል በሽብር ወንጀል እንደከሰሳቸው ይታወቃል።

ችሎቱ በግለሰቦቹ ላይ ለዛሬ ክስ ለመመልከት ነበር ቀጠሮ ይዞ የነበረው፤
ይሁን አንጂ ሶስቱ ተከሳሾች ከዳንሻና አዋሽ ማቆያ ሌሎችም ከቃሊቲ ማቆያ በመረጃ ልውውጥ ስህተት ሊቀርቡ አልቻሉም ተብሏል።

በዚሁ መሰረት የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ በትክክል ተተግብሮ በአካል የሚቀርቡ 20 ተከሳሾች ለጥቅምት 3፣ 2014 ቀርበው ክስ እንዲነበብ ሲል ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

በዚሁ ቀን እነ ሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ ጨምሮ ያልተያዙ 54 ተከሳሾች በፌዴራል ፖሊና በመከላከያ በትብብር ተይዘው እንዲቀርቡ ሲል ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ አስተላልፏል መባሉን ብሔራዊ ቴሌቭዥን ዘግቧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img