Saturday, November 23, 2024
spot_img

ታሊባን ለአፍጋኒስታን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ምህረት ማድረጉን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 11፣ 2013 ― የአፍጋስታን ዋና ከተማን ካቡልን ተቆጣጠረው የታሊባን ቡድን ለቀድሞ አፍጋኒስታን መንግስት የስራ አመራሮች ምህረት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ለሁሉም የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ምህረት አድርጌያለሁ ያለው ታሊባን፤ ሁሉም የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ወደ ስራቸው እንዲመለሱም ጥሪ አቅርቧል።

ታሊባን አዲስ ያሳለፈው ውሳኔ ቡድኑ በትላትናው እለት በአፍጋኒስታን ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ሰብአዊ ድጋፍ ድርጅቶች እና የውጭ ሀገራት ዲፕሎማቶች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ቃል መግባቱን ተከትሎ የተደረገ ነው ተብሏል፡፡

የአሜሪካ እና የሰሜን አትላቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ከአፍጋኒስታን ለቆ መውጣት ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ታሊባን የአፍጋኒስታንን በርካታ ግዛቶች መቆጣጠሩ ይታወቃል።

ባለፉት 3 ወራ በርካታ የሀገሪቱን ግዛቶች በቁጥጥር ስር ያዋለው ታሊባን ባሳለፍነው እሁድ የሀገሪቱን ዋና ከተማ ካቡልን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

በሁኔታው የተደናገጡ መንግስት ሰራተኞች ቢሯቸውን ለቀው መውጣታቸው የተነገረ ሲሆን፤ በርካታ የአገሪቱ ዜጎች የሚከሰተውን ነገር በስጋት ውስጥ ሆነው እየተጠባበቁ እንደነበር ነው ተገልጧል።

የታሊባን ታጣቂዎች ካቡልን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ ሀገሪቱን ለቀው መውጣታቸው መነገሩም ይታወቃል።

ካቡል በታሊባን እጅ መውደቋን ተከትሎ በርካታ አፍጋናውያንና የሌሎች ሃገራት ዜጎች በካቡል ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል ለቀው ለመውጣት ሲያደርጉ የተስተዋሉት ትንቅንቅ ብዙዎችን አስገርሟል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በትናትናው እለት በሰጡት መግለጫ ሀገሪቱ በታሊባን እጅ ለማደቋ የአፍጋኒስታን አመራሮችን ወቅሰዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img