Tuesday, October 15, 2024
spot_img

የዓለማችን ዋነኛ ቱጃር ጄፍ ቤዞስ ናሳን ሊከስ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 11፣ 2013 ― የጄፍ ቤዞስ የሕዋ ምርምር ተቋም ብሉ ኦሪጂን፤ ናሳ የተሰኘው የአሜሪካው የሕዋ ተቋምን ሊከስ እንደሆነ ተሰምቷል።

ናሳ ሉናር ላንደር የተሰኘ ቴክኖሎጂ እንዲሠራለት ጨረታ አውጥቶ ለኢላን መስክ ድርጅት የ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ኮንትራት መስጠቱን ተከትሎ ነው ብሉ ኦሪጂን ክስ ሊመሠርት የተሰናዳው።

የቤዞስ ብሉ ኦሪጂን በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የተገባው ስምምነት “ችግሮች አሉበት”፤ አልፎም ፍትሃዊ አይደለም ሲል ወቅሷል።

ናሳ ቅድሚያ አቅዶ የነበረው ሥራውን ለሁለት ድርጅቶች ለመስጠት ነበር።

ነገር ግን ባለፈው ሚያዚያ ጨረታውን ካወጣ በኋላ በበጀት እጥረት ምክንያት ለአንድ ድርጅት መስጠቱን ተናግሮ ነበር።

ምንም እንኳ ናሳ እስካሁን በክሱ ዙሪያ አስተያየት ባይሰጥም አንድ ብሔራዊ ተቋም ይደግፈዋል እየተባለ ነው።

ባለፈው አርብ ክሱን የመሠረተው ብሉ ኦሪጂን ሁለት ተቋማት ቴክኖሎጂውን ለመገንባት ያስፈልጋሉ የሚል እምነት እንደነበረው በክስ መዝገቡ ላይ አስፍሯል።

ናሳ ሊያሠራ ያሰበው ቴክኖሎጂ የጠፈር ተመራማሪዎችን ይዞ ወደ ጨረቃ የሚያቀና መንኩራኩርን ለማሳረፍ የሚውል ነው።

የአሜሪካ ሕዋ ምርምር ተቋም ናሳ ይህን ቴክኖሎጂ በፈረንጆቹ 2024 ለመሞከር አቅዷል። ነገር ግን ብሉ ኦሪጂን በጨረታው ሂደት ናሳ “ሕጋዊ ያልሆነ ግምገማ አድርጎብናል” ሲል ከሷል።

ናሳ ጨረታውን ማን እንዳሸነፈ ይፋ ባደረገበት ወቅት የተቋሙ ‘ሂዩማን ኤክስፕሎሬሽን’ አለቃ የሆኑት ካቲ ሉደርስ ናሳ ሁለት ኩባንያዎችን ከመቅጠር የተቆጠበው በበጀት እጥረት ምክንያት ነው ብለው ነበር።

ናሳ ለፕሮጀክቱ ማስኬጃ 3.3 ቢሊዮን ዶላር ከመንግሥት ቢጠይቅም ኮንግረሱ 850 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው የፈቀደው።

ስፔስኤክስ የተባለው የኢላን መስክ ተቋም የተሳኩ የኦርቢት [ምህዋር] ሚሽኖች ማካሄዱ እንዲመረጥ እንዳደረገው ናሳ ተናግሮ ነበር።

ነገር ግን ስፔስኤክስ ከሌሎች ተቋማት ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስ ያለ ገንዘብ ማቅረቡ ጨረታውን እንዲያሸንፍ እንዳገዘው እየተነገረ ነው። ባለፈው ወር ጄፍ ቤዞስ ናሳ ያጠረውን 2 ቢሊዮን ዶላር ከፍሎ በፕሮጀክቱ መካተት እንደሚፈልግ ቢናገርም ሐሳቡ ተቀባይነት አላገኘም።

የመንግሥት ተጠያቂነት ቢሮ የተሰኘው የአሜሪካ ፌዴራላዊ ተቋም ግን የብሉ ኦሪጂንና ዳይኔቲክ የተሰኘውን ሌላ የሕዋ ተቋም ክስ አጣጥሎታል።

ናሳ እስከ ጥቅም 2/2015 ባለው ጊዜ ውስጥ ምላሽ መስጠት አለበት የተባለ ሲሆን፣ የኢላን መስክ ስፔስኤክስ እካሁን ምንም አስተያየት አልሰጠም መባሉን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ናሳ በአዲሱ ቴክኖሎጂ ታግዞ ከፈረንጆቹ 1972 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጨረቃ ለመመለስ አቅዷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img