Wednesday, October 16, 2024
spot_img

በሶማሌ ክልል ሁከትና ግጭት የማስነሳት ሙከራ መክሸፉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 10፣ 2013 ― የሶማሌ ክልል ፖሊስ በክልሉ ለውጥ በመምጣቱ “ጥቅማቸውን ያስቀረባቸው” ያላቸው ሀይሎች ከሕወሓት ጋር ኔትወርክ በመፍጠር ሁከትና ግጭት ለማስነሳት ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ሕወሓት በስልጣን በነበረበት ጊዜ የሱማሌ ክልል ሕዝብን “አብረውት ሲዘርፉና ሲያዘርፉ የነበሩና ለውጥ ከመጣ በኋላ ከስልጣን የተወገዱ የቀድሞ አስተዳደር ርዝራዦች” ያላቸው ከህውሓት ተልእኮ በመቀበል የሀይማኖት እና የጎሳ ግጭት በመፍጠር የከተማ ውስጥ አመፅ ለማቀጣጠል እንዲሁም በሶማሌና በኦሮሞ መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበርም ነው ያመለከተው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img