Wednesday, October 16, 2024
spot_img

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኦነግ ሸኔ ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚገናኝውን መንገድ አዘጋለሁ የሚል ማስጠንቀቂያው አይሳካም አለ::

በሽብርተኛነት የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገር ኬንያ ጋር የሚያገናኘውን መንገድ እዘጋለሁ ማለቱ መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የቡድኑ እቅድ አይሳካለትም ብሏል፡፡

የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለአሻም ቲቪ እንደተናገሩትም የክልሉ የፀጥታ ሀይል ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በሽብርተኝነት የተፈረጀውን የኦነግ ሽኔ ሀይል እየደመሠሠ ይገኛል፡፡

በተያያዘ ይኸው ታጣቂ ቡድን በምዕራብ ኦሮሚያ ላይ የትራንስፖርት መስተጓጎል ስለመፍጠሩ በኬንያው ኔሽን ጋዜጣ ተዘግቦ ነበር፡፡

ነገር ግን የቢሮው ኃላፊ ቡድኑ ለማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንዲውል መንገዶችን ይዘጋል፤ ፎቶም ይነሳል እንጂ በተነገረው መጠን ቡድኑ የፈጠረው እክል የለም ሲሉ መልሰዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img