Friday, October 11, 2024
spot_img

የኤርትራ እና የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሪያድ ውይይት አደረጉ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 8፣ 2013 ― የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ ከሳዑዲ ዓረቢያው አቻቸው ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን ቢን ዐብዱላህ ጋር በትላንትናው ዕለት በሳዑዲ ዋና ከተማ በሪያድ ተገናኝተው መምከራቸው ተሰማ።

በውይይቱም የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን እና የሁለቱን አገራት ጥቅሞች ለማስጠበቅ በሁሉም መስኮች ማሳደግ የሚችሉባቸው መንገዶች ላይ እንደተወያዮ ታውቋል።

በተጨማሪም ለደኅንነት እና መረጋጋት መሠረቶችን ለመጣል፣ ግጭቶችን ለመፍታት፣ ልማትን ለማፋጠን እና በአፍሪካ ውስጥ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ የሳውዲ መንግስት ያደረገውን አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጥረት እና ድጋፍ መገምገም ችለዋል።

አክለውም ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃዎች ስለተመዘገቡ ለውጦች እና በጋራ ጥቅም ጉዳዮች ላይና በቀጣይ በጋራ መስራት የሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img