Sunday, October 6, 2024
spot_img

ፖሊስ በሕገ ወጥ መንገድ በአንድ መኖሪያ ቤት ተከማችቶ የተገኘ ከ15 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር መያዙን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 7፣ 2013 ― የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሕገ ወጥ መንገድ በአንድ መኖሪያ ቤት ተከማችቶ የተገኘ ከ15 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር መያዙን አስታውቋል፡፡

እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ ወንጀሉ የተፈፀመው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ሃያ ሁለት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፣ ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አንድ አካል በሆነው ወንጀልን እና ወንጀለኞችን የመቆጣጠር እንቅስቃሴ ከላይ በተጠቀሰው ስፍራ በሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ጥናትና ክትትል ከተደረገ በኋላ ነሐሴ 5፣ 2013 ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማዉጣት በተደረገዉ ብርበራ በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ 158 ባለ መቶ የአሜሪካ ዶላር ወይም 15 ሺሕ 800 የአሜሪካ ዶላር ሊያዝ ችሏል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በዋለው ግለሰብ ላይ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የገለጸው ፖሊስ፣ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይል ጋር በጋራ በመስራት መሠል ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ክምችትን ለመከላከል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ በመቀጠል በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት በመታደግ የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img