Monday, October 14, 2024
spot_img

የጤና ሚኒስቴር ለኮቪድ 19 የሚደረገው ጥንቃቄ መዘናጋት አሳስቦኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 5፣ 2013 ― በአገሪቱ ለኮቪድ 19 የሚደረገው ጥንቃቄ መዘናጋት እንዳሳሰበው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ እንደገለጹት የህብረተሰቡ መዘናጋትና ቸልተኝነት የሚያሳስብ ሆኗል፡፡

ዶክተር ደረጄ መንግስት ዜጎች እንዲጠነቀቁ ለማድረግ የተለያዩ ንቅናቄዎችን እያደረገ ቢሆንም ማህበረተሰቡ ተዘናግቷል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የቫይረሱ ስርጭት ከዚህ በፊት ከነበረው አሁን ቁጥር ጨምሯል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ የጽኑ ህሙማን ክፍሎችም እየተጨናነቁ ናቸው ብለዋል፡፡

የኮቪድ 19 ምርምራ አሁን ላይ በርካታ ሰዎች በሚገኙበት ቦታ እና በኬላዎች አካባቢ ላይ ተጠናከሮ መቀጠሉንም የተነገሩት ሚኒስትር ዲኤታው፣ በቀጣይ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች ትኩረት እንዲያደረጉ የተለየ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙም ነው የገለጹት፡፡

አያይዘውም የመተንፈሸ መሳሪያዎች እጥረት እና ህክምና መስጫ ተቋማት እየሞሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል መባሉን የዘገበው ፋና ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img