Monday, October 14, 2024
spot_img

በጋሊኮማ በንፁሐን አርብቶ አደሮች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአፋር ክልል የሦስት ቀን ሐዘን ታወጀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 5፣ 2013 ― የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በፈንቲ ረሱ በጋሊኮማ ጊዚያዊ መጠለያ በሕወሓት ተፈጽሟል ያለውን ጥቃት ተከትሎ ከዛሬ ጀምሮ የሦስት ቀን ሐዘን ማወጁን አሳውቋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አሚና ሴኮ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ሕወሓት በጋሊኮማ በንፁሀን ላይ አድርሶታል ያሉት ‹‹ጭፍጨፋ እጅግ ዘግናኝ እንደነበር›› ገልፀው፣ የክልሉ መንግስትም ይህንኑ አስመልክቶ የሶስት ቀናት ሐዘን አውጇል ብለዋል፡፡

የአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ባወጣው መረጃ መሠረት በጥቃቱ 107 ሕፃናትን ጨምሮ 89 ሴቶች እና 44 አዛውንቶች ሕይወታቸውን ተነጥቀዋል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ሕወሓት በድንገት በከባድ መሳሪያ ታግዞ አድርሶታል ባለው ጥቃት ‹‹ንፁሃን አርብቶ አደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው እንዲሁም በመጋዝን የነበረ የአስቸኳይ እርዳታ ሙሉ በሙሉ መውደሙንም›› አስታውሷል፡፡

የሦስት ቀናት የሐዘን ጊዜ ያወጀው የአፋር ክልል ‹‹የዘር ማጥፋት›› ያለውን ድረጊት፣ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በያሉበት ሆነው እንዲቃወሙና እንዲያወግዙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጥቃቱን አድርሷል ተብሎ በክልሉ መንግሥት የተወነጀለው ሕወሓት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img