Monday, September 23, 2024
spot_img

ጊኒ በምዕራብ አፍሪካ የመጀመሪያውን በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው አገኘች

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 4፣ 2013 ― የጊኒ የጤና ባለሥልጣናት በምዕራብ አፍሪካ የመጀመሪያውን በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን አረጋግጠዋል።

ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ተላላፊ የሆነና ኢቦላን ከሚያስከትለው ቫይረስ ጋር በተመሳሳይ ዝርያ ውስጥ መሆኑም ተነግሯል፡፡

የማርበርግ የቫይረስ በሽታ ወደ ሰዎች የሚተላለፈው ከሌሊት ወፎች ሲሆን፣ 88 በመቶ የመግደል አቅም አለው የተባለው ቫይረስ ከሰው ወደ ሰውም የሚተላለፈው በሰውነት ፈሳሾች አማካኝነት ነው፡፡

ቫይረሱ ትኩሳት እና የደም መፍሰስ ችግርን የሚያመጣ ከባድ ገዳይ በሽታ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅትም ቫይረሱ ሳይዛመት ‹‹በጅምሩ መቆም›› እንዳበተ አስጠንቅቋል፡፡

በጊኒ በቫይረሱ ከተያዘው ግለሰብ የተወሰዱ ናሙናዎች በአገሪቱ ላቦራቶሪዎች ውስጥ ተመርምረው የማርበርግ ቫይረስ እንዳለበት እንደተረጋገጠ ሲነገር፣ በቫይረሱ የተያዘው ግለሰብም ሐምሌ 26፣ 2013 ህይወቱ አልፏል።

የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ማትሺዲሶ ሞኤቲ ቫይረሱ በሰፊው የመሰራጨት አቅም እንዳለው ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎችን ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው።

የቅርብ ጊዜ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በጊኒ እና በአጎራባች አገሮች ውስጥ ተዘርግተው የነበሩ ስርዓቶች የማርበርግ ቫይረስንም ከመዛመት ለመከላከል ተግባራዊ እየሆኑ ነው ተብሏል።

የማርበርግ ቫይረስ እስካሁን ድረስ የመከላከያ መድሃኒት የሌለው መሆኑንም የዓለም ጠየና ድርጅት አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img