Monday, October 14, 2024
spot_img

የአማራ ክልል ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ አድርጎ ሾመ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 14፣ 2013 ― የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የሥራ ምደባ ሰጥተዋል።

የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ከርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ተነግሮኛል እንዳለው ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበዋል።

ሌሎች ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ልዩ ልዩ የጸጥታ ተቋማትን እንዲመሩ በርእሰ መሥተዳድሩ ምደባ መሰጠቱንም ዘገባው አክሏል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img