Monday, October 14, 2024
spot_img

በባልደራስ አመራሮች ላይ የማቀርባቸው ምስክሮች ጥበቃ ይደረግላቸው የሚለው የዐቃቤ ሕግ ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሐምሌ 8፣ 2013 ― የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ ሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ዛሬ ባስቻለው ችሎት ላይ ነው፡፡

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ከአንድ እስከ አራት ያሉት ተከሳሾች ጠበቃ አቶ ቤተ ማርያም ዐለማየሁ ነግረውኛል ብሎ አሻም ቲቪ እደዘገበው፣ ዐቃቤ ሕግ ለምስክሮቹ ሦስተኛ ወገን ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹ ከመጋረጃ ጀርባ ምስክርነታቸውን ይሰጡ ብሎ ቢጠይቅም በተመሳሳይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ማደረጉን ጠበቃው አስታውሰዋል፡፡

ሰኔ 22፣ 2013 በዋለው ችሎት ዐቃቤ ህግ ለሐምሌ 8፣ 9፣ 14፣ 15 እና 16 ቀን 2013 ዓ.ም. 21 ምስክሮች ቃላቸውን እንዲሠጡ ቀጠሮ አስይዞ ነበር፡፡

ይሁንና ዐቃቤ ሕግ ዛሬ ባስቻለው ችሎት ለምስክሮቹ ጥበቃ ያስፈልጋል፤ ለዚህ ደግሞ በጀት ያስፈልጋል የሚል መከራከሪያ ሀሳብ አንስቷል፡፡

የተከሳሾች ጠበቃ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ ይህን መከራከሪያ ሳይቀበለው የቀረ ሲሆን፣ በዚህም ከሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓጀምሮ ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን እንዲያሰማ ማዘዙን አክለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img