Monday, October 14, 2024
spot_img

ኢትዮጵያውያኑ እናት እና ልጅ ማሪዋና በማዘዋወር እና መሸጥ ተጠርጥረው ተያዙ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ― በአሜሪካ ዳኮታ ነዋሪ የሆኑት ኢትዮጵያውያኑ እናት እና ልጅ አዳነች መልካ አበራ እና ምስክር አሻሜ መንግሥቱ ማሪዋና በማዘዋወር እና መሸጥ ተጠርጥረው እንደተያዙ ዳኮታ ኒውስ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን የያዘው በሳምንቱ መጀመሪያ ከአንድ ሥፍራ የጥይት ተኩስ መሰማቱን ተከትሎ ተጠርጣሪዎቹ በሚኖሩበት አፓርትመንት የአደንዛዥ እዝ ክትትል ቡድን ባደረገው ፍተሻ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

ፖሊስ ባደረገው ፍተሸ በ21 ዓመቱ ምስክር አሻሜ መንግስቱ እጅ ሽጉጥ ማግኘቱ ሲነገር፣ በተጨማሪም በቤቱ ውስጥ 10 ፓውንድ የማሪዋና ጥቅሎች በመገኘቱ እናት እና ልጅ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዳኮታ ኒውስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ፖሊስ የጦር መሳሪያ ይዞ አግኝቼዋለሁ ያለውን ወጣት ከባድ ወንጀል ለመፈፀም መሞከር በሚል እና በቸልተኝነት መሳሪያ በመጠቀም እንዲሁም አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር እና በመሸጥ ጠርጥሬዋለሁ ያለ ሲሆን፣ እናትየውን ደግሞ አደንዛዥ እጽ በማዘዋወር እና በመሸጥ በሚል ይዟል፡፡

የ48 ዓመት እድሜ ያላቸው አዳነች መልካ አበራ በሱፎልስ ሳውዝ ዳኮታ ከሃያ ዓመት በላይ መኖራቸው ሲነገር፣ በስጋ ማቀነበበርያ ኩባንያ ውስጥ የሚሠሩና የተመሰገኑ መሆናቸው ተነግሮላቸዋል፡፡

ወይዘሮ አዳነች ከአራት ዓመታት በፊት የመጀመርያ ልጅ ሚካኤል መንግስቱ አሻሜ በጓደኛሞች መካከል በተካሄደ ተኩስ በመሞቱ ለበሐዘን ውስጥ መቆየታቸውን የሚያውቋቸው ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img