Monday, November 25, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ በእስራኤሉ ኩባንያ የተመሠረተባትን ክስ በሔግ ፍርድ ቤት ረታች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 3፣ 2013 ― በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ በሄግ ኔዘርላንድስ ቋሚ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት ክስ የመሠረተው የእስራኤሉ እስራኤል ኬሚካል ሊሚትድ ኩባንያ በኢትዮጵያ መንግስት ተረቷል፡፡

መቀመጫውን በሄግ ኔዘርላንድስ ያደረገው ቋሚ የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት በትላንትናው ዕለት ክሱን ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ፣ ኢትዮጵያ እንድትከፍል ከተከሰሰችበት የመቶ ሚሊዮኖች ዶላር ነፃ ተደርጋለች።

ኩብንያው ኢትዮጵያንና የማዕድን ሚኒስቴርን አጣምሮ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የከሰሰው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኝ ሐብት ላይ ኩባንያው በውጭ ሀገር ለፈፀመው ግዢ የካፒታል ጌይን እና የተጨማሪ እሴት ታክስን እንዲከፍል የኢትዮጵያ የገቢዎች ሚኒስቴር በመወሰኑ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የዓለም አቀፍ ሕግን (የኔዘርላንድስንና የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ የኢንቨስትመንት ጥበቃ ስምምነት) ጥሷል በሚል ነው።

ከሳሹ ታክስ ተጣለብኝ ይበል እንጂ የኢትዮጵያ የገቢዎች ሚኒስቴር ታክሱን በወቅቱ ጥሎ የነበረው በሻጩ ኢትዮጵያዊ ኩባንያ በአላና ፖታሽ አፋር ላይ ነበር።

ከታመኑ ምንጮች በተገኘው መረጃ መሰረት አራት ዓመታትን የፈጀው ዓለም አቀፍ ክርክር በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። የፍርድ ቤቱም ውሳኔ የተላለፈው በሙሉ ድምፅ ነው ሲሆን፣ ውሳኔው ይግባኝ የማይባልበት ነው።

በዓለም ታዋቂና ስመጥር የሆኑ ዳኞች የሚገኙበትን ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በሰብሳቢ ዳኝነት የመሩት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት የተከበሩ አሜሪካዊት ዳኛ ጆን ዳናሁዌ ናቸው።

ሁለቱ የቀኝና የግራ ዳኞችም እንዲሁ ከፍተኛ ስም ያላቸው የተከበሩ የዘርፉ ባለሙያዎች ናቸው፤ ፕሮፌሰር ሺያን መርፊ በአሜሪካ በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲት ታዋቂ የህግ ፕሮፌሰርና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለምአቀፍ ሕግ ኮሚሽን አባል ሲሆኑ፤ ሚ/ር ሮበርት ስሚዝ ደግሞ በኒው ዮርክ በግል የግልግል ዳኛ በመሆን የበርካታ አስርት ዓመታት የሥራ ልምድ ያላቸው ናቸው።

በሄጉ የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በነበረው የክርክር ሂደት ከሳሽ ተወክሎ የነበረው ሗይት ኤንድ ኬዝ በሚባለው በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘውና ኸርበርት ስሚዝ ፍሪሂልስ በሚባለው በኒው ዮርክ በሚገኘው ሁለት ዓለም አቀፍ የህግ ቢሮዎች ነው።

ኢትዮጵያን በመወከል የተከራከረው ደግሞ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው አዲስ ሎው ግሩፕ ኤል ኤል ፒ የተባለውና በኢትዮጵያውያንና በትውልደ ኢትዮጵያውያን የተመሰረተና የሚመራው ዓለም አቀፍ የህግ ቢሮ መሆኑንም የዘገበው ሪፖርተር ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img