Thursday, November 21, 2024
spot_img

የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት እጄን አልሰጥም ማለታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሰኔ 28፣ 2013 ― የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በህግ ቁጥጥር ስር የሚውሉበት ቀን እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ዙሪያ ለተሳበሰቡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው መብታቸው መጣሱን ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ፕሬዝዳንቱ እጃቸውን ለፖሊስ እንዲሰጡ የ5 ቀናት ቀነ ገደብ ማስቀመጡን አስታውቋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ ፍርድቤቱ ለሚያደርገው የሙስና ወንጀል ምርመራ መረጃ ለመስጠት ሲጠየቁ በተደጋጋሚ ባለመተባበራቸው፣ ለፍርድቤቱን ንቀት አሳይተዋል በሚል የ15 ወራት እስር ተላልፎባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ነገር ግን ፕሬዘዳንቱ የሚታሰሩ ከሆነ ደጋፊዎቻቸው በደቡብ አፍሪካ አመጽ እናስነሳለን ሲሉ ዝተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በፕሬዘዳንቱ ላይ ፍርድ ካስተላለፈ በኋላ የፕሬዘዳንቱን አቤቱታ ሊቀበል እንደሚችል አስታውቋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ እጅ የሚሰጡበት ጊዜ በመጭው እሁድ የሚያበቃ ቢሆንም የ79 አመቱ ጃኮብ ዙማ እጅ ለመስጠት ያሳዩት ምልክት የለም፡፡

‹‹እዚህ ፖሊሶችን ሳይ እንዴት እንደሚይዙኝ ይገርመኛል፣ እንዴት ይህን ሁሉ ሰው አልፈው ይይዙኛል›› በማለት ጃኮብ ዙማ በደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት ላይ ማሾፋቸውን ቀጥለዋል፡፡

ፕሬዘዳንት ዙማ እጅ ለመስጠት ፍቃደኛ ካልሆነ ፖሊስ ተጨማሪ ሶስት ቀናት ጊዜ ይሰጣቸዋል የተባለ ሲሆን፣ ቻትሊን ፖዌል የተባሉ የደቡብ አፍሪካ የህግ ፕሮፌሰር ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት የዙማን አቤቱታ መስማት የህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቱን ወሳኔ አያስቆመውም ማለታቸውን አል ዓይን ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img