Sunday, October 13, 2024
spot_img

በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች ቤተሰቦች ምግብ እና አልባሳት ማቀበል አልቻልንም ማለታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ሰኔ 27፣ 2013 ― ከሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት አንስቶ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች ቤተሰቦች ምግብ እና አልባሳት ማቀበል አለመቻላቸውን መስማቱን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ አሳውቋል።

በተጨማሪም የጋዜጠኞቹ ጠበቃ የሆኑት ታደለ ገብረመድኅን ማግኘት አለመቻላቸውን ያመለከተው ሲፒጄ፣ እስካሁን ድረስም ፍርድ ቤት አልቀረቡም ብሏል።

ባለፉት ቀናት በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ ጋዜጠኞች መካከል የኢትዮ ፎረሞቹ አበበ ባዩ፣ ያየሰው ሽመልስ እንዲሁ የአውሎ ሚዲያው በቃሉ አላምረው ይገኙበታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img