አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሰኔ 24፣ 2013 ― በትግራይ ግጭት ወድመው የነበሩ እና አዳዲስ የሕክምና ቁሳቁስ አቅርቦቶችን ያገኙ አንዳንድ የጤና ተቋማት ዳግመኛ መዘረፋቸውን ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ድርጅት አስታውቋል።
የሐኪሞች ቡድኑ የጤና ተቋሚቱ በማን እና እንዴት እንደተዘረፉ ያለው ነገር የለም።
የድንበር የለሽ የሐኪሞች ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ ማሪ ካርመን ቪዮለስ እንዳሉት፣ በትግራይ ክልል ከ 75 በመቶ በላይ የህክምና ተቋማት ወድመዋል ወይም ተዘርፈዋል እንዲሁም በክልሉ 5.5 ሚሊዮን ሰዎች ለአስቸኳይ የምግብ ዋስትና ተጋልጠዋል።
ዓለም አቀፉ የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ከሳምንት በፊት ባልደረቦቹ ትግራይ ውስጥ «በጭካኔያዊ ሁኔታ ተገድለው» መገኘታቸውን ማሳወቁ አይዘነጋም።