Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ ተከሳሾች ላይ ብይን ተሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሰኔ 11፣ 2013 ― ዛሬ አርብ ማለዳ የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዋለው ችሎት በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ እጃቸው አለበት የተባሉ 55 ተከሳሾች ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሻምበል መማር ጌትነት የክስ መዝገብ ስማቸው የተዘረዘሩ 55 ተከሳሾች ውስጥ 6ቱ በሌሉበት፣ 49 በተገኙበት ፍርዳቸው ሲታይ የነበረ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ አቶ ዘመነ ካሴን ጨምሮ 20ዎቹን በነጸ አሰናብቷል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በሕዝብ ደህንነት ላይ ሁከት በመፍጠር፣ የክልሉን አመራሮች በመግደል፣ የሕዝብ ኑሮና ደኅንነት ላይ አደጋ በመፍጠር፣ በሕገ መንግስት የተቋቋመ ስርዓት ለማፍረስ በመሞከር፣ የክልሉን ስልጣን ለመቆጣጠር ግብ ያደረገ እንደነበርና ለዚህም ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ የክልሉን መገናኛ ብዙኃን ጨምሮ ዋና ዋና ተቋማትን በመቆጣጠር ሥልጣን ለመያዝ አቅደው ነበር ብሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ በ31 ተከሳሾች ላይ ሐምሌ 5 የክስ መቃወሚያ እና መከላከያ ምስክር እንዲያሰሙ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ሰኔ 15፣ 2011 ‹‹በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ›› ሕይወታቸውን ካጡት መካከል የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አምባቸው መኮንን እንደሚገኙበት የሚታወቅ ነው፡፡

ችሎቱ በዛሬው እለት የጥፋተኝነት ብይን የሰጠው ለሁለት ዓመታት ያህል ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቶ መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img