Sunday, September 22, 2024
spot_img

በ‹ፕሮፐርቲ 2000› ላይ የሐሰት ወሬዎች እየተናፈሱበት ነው ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ግንቦት 30፣ 2013 ― ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ 500 ሺሕ መኖሪያ ቤቶችን በአምስት ዓመታት ለመገንባት ከከተማው አስተዳደር ጋር ስምምነት የደረሰው ፕሮፐርቲ 2000 የተሰኘው የደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ላይ የሚናፈሱ ወሬዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን የከተማዋ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የግንባታ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃርሶ ጎሊሳ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር የተደረሰው ስምምነት ሕጋዊ ሂደቶችን ያለፈ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሆኖም ከደቡብ አፍሪካው ‹ፕሮፐርቲ 2000› ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ‹ሐሰተኛ መረጃዎች› በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኩባንያው ከ31 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው መሆኑንና በኢትዮጵያ ለመሰማራት ከሦስት አመታት በላይ ፍላጎቱን ሲያሳይ መቆየቱንም ነው የገለጹት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሐሰተኛ መረጃ እየተናፈሰበት ነው ያለው የደቡብ አፍሪካው ፕሮፐርቲ 2000 ከተቋቋመ 31 ዓመት ያስቆጠረ ነው ቢባልም፣ ስለ ኩባንያው የተጻፉ መረጃዎች የሚያመለክቱት ግን ደቡብ አፍሪካ ብሎምፎንቴን ከተማ የተመዘገበው ፕሮፐርቲ 2000፣ በኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ኅዳር ወር 2011 የተመዘገበ ነው፡፡

ኩባንያው ከዚህ ቀደም በሌሴቶ ከስታዲየም ግንባታ ጋር በተገናኘ ለሦስት የአገሪቱ ተቋራጮች ብድር ለማመቻቸት ገንዘቡን እቀበልበታለሁ ያለው የእንግሊዝ ባንክ ያልተመዘገበ ነው በሚል ውሉ የተሰረዘበት መሆኑንም መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img