Thursday, October 10, 2024
spot_img

በመቀሌ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በኦክስጅን እጥረት የታካሚዎች ሕይወት አለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 26፣ 2013 ― በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሚገኘው ዓይደር ሆስፒታል ሃያ ሁለት ታካሚዎች በኦክስጅን እጥረት ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ሆስፒታሉ አስታውቋል፡፡

የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ገብረሥላሴ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት ቀድሞም ቢሆን 2013 ከገባ ጀምሮ ከፍተኛ የማምረት አቅም እጥረት እንደገጠማቸው አስታውሰው፣ በክልሉ ጦርነቱ ጥቅምት ላይ ሲጀምር ለሆስፒታሉ በነጻ ኦክስጅን ያቀርብ የነበረው ቬሎሲቲ የተባለ ጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ በመውደሙ ችግር ገጥሟቸዋል፡፡

ኋላም በጤና ሚኒስቴር ገንዘቡ እየተሸፈነ በግል በግዢ ቢቀጥሉም ከአንድ ወር በፊት ግን የግል ድርጅቱ የኦክስጅን ማሽኑ ችግር እንደገጠመው ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

የድርጅቱን የማሽን ብልሽት ተከትሎም ከአዲስ አበባና ደሴ ለማምጣት ቢሞከርም በመንገድ መዘጋጋትና ሌሎችም ምክንያቶች ሊደርስ አልቻለም፡፡

በሁኑ ወቅት የራሳችንን ለመጠገን ሙከራ እያደረግን ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፣ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት ትልቅ ማሽን ለመትከል ከፌዴራል መንግስት ጋር እየተነጋገርን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img