Thursday, October 10, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ ሰበር ሰሚ ችሎት ለባልደራስ የወሰነውን ለምን እንዳልፈጸመ ነገ ቀርቦ ያስረዳል ተብሎ ተጠብቋል

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 25፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እነ አቶ እስክንድር ነጋ በዕጩነት እንዲመዘገቡ የሰጠውን ውሳኔ ለምን መፈጸም እንዳልቻለ ነገ ሐሙስ ግንቦት 26፣ 2013 በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ ያስረዳል ተብሎ ተጠብቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ ለቦርዱ ትዕዛዙን ያስተላለፈው ሰኞ ግንቦት 23፣ 2013 ሲሆን፣ ለትዕዛዙ መነሻ የሆነው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ)፣ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ፣ ቦርዱ ‹‹አልፈጽምም›› ማለቱን ገልፆ፣ እስከሚፈጽም ድረስ ሰኔ 14፣ 2013 እንዲካሄድ የተወሰነው አገራዊ ምርጫ እንዲታገድለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ፓርቲው ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ባቀረበው አቤቱታ፣ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ ቦርዱ ለመፈጸም እምቢተኛ መሆኑን ጠቁሞ፣ ዕጩዎቹ በተወዳዳሪነት ሳይመዘገቡ ድምፅ ቢሰጥ፣ መብቱን በእጅጉ ከመንካቱም በላይ፣ ፍርድ ቤቶች በምርጫ ጉዳይ የሚሰጡት ውሳኔ ‹‹ተፈጻሚነት አይኖረውም›› የሚል ጥርጣሬ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ እንደሚያሳድር በማስረዳት፣ ምርጫው እንዲታገድለት አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img