Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በነ ጀዋር መሐመድ ጉዳይ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባሉ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 19፣ 2013 ― የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ዶክተር ጌድዮን ጢሞቴዎስ እነ ጃዋር መሐመድ ለ40 ቀናት ያህል የረሀብ አድማ ላይ በነበሩበት ጊዜ በላንድ ማርክ ሆስፒታል ሊደረግላቸው የሚገባውን የሕክምና ክትትል በማስተጓጎል እና የፍርድ ቤትን ትእዛዝ በማስተጓጎል በሚል በቀረበባቸው ክስ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መባላቸውን የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል፡፡

ዛሬ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ክሳቸውን ለመከታተል በአካል የቀረቡት ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ ለቀረበባቸው ክስ ‹‹በወቅቱ የፍርድ ቤቱን ትዛዝ የጣስኩት የጸጥታ ስጋት ስለነበር፣ የሕዝብ ጥቅም እንዳይጎዳ እና ይግባኝ ለመጠየቅ ጊዜ ስላልነበረ ነው›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የነ ጃዋር መሐመድ ጠበቃ የሆኑት አቶ ሚልኪያስ ቡልቻ ‹‹በወቅቱን ምንም ዐይነት የደኅንነት ስጋት አልነበረም፣ ቢኖርም ሕክምናው የሚደረገው ከተማ ውስጥ ስለነበር ከመንግስት አቅም በላይ የሚሆን አይደለም እንዲሁም አቃቢ ህግ የፍርድ ቤትን ውሳኔ የሚለውጡበትም ሆነ የሚያስቆሙበት የህግ አሰራር የለም። ስለዚህ ችሎትን በመድፈር ወንጀል ሊቀጡ ይገባል›› በማለት ተከራክረዋል።

የሁለቱንም ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤት ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን ችሎትን በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ናቸው ሲል ብይን ሰጥቷል። ነገር ግን ቅጣትን በተመለከተ የመጀመሪያቸው ስለሆነ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በመስጠት አልፏቸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img