Monday, November 25, 2024
spot_img

በአክሱም የአገር መከላከያ ሠራዊት ወታደሮች የሕወሓት ተዋጊዎችን ፍለጋ ሆስፒታል መፈተሻቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ግንቦት 12፣ 2013 ― የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ባለፈው እሑድ ትግራይ አክሱም ከተማ ውስጥ ወደሚገኝ ሆስፒታል ገብተው ፍተሻ ማድረጋቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ወታደሮቹ በከተማዋ ውስጥ ወደሚገኘው ሆስፒታል የገቡት የህወሓት ተዋጊ አባላትን ለመፈለግ እንደሆነ የዜና ወኪሉ ሐኪሞችን ዋቢ አድርጓል፡፡

አዣንስ ፍራራስ ፕረስ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩና ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የጤና ባለሙያዎች ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው፤ ወታደሮቹ ዶክተሮች፣ ነርሶችና ቁስለኛ ታካሚዎች ላይ መሳሪያ በመደገን ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበር።

ዋቢ የተደረጉት የጤና ባለሙያዎች ወታደሮቹ ‹‹ታካሚዎቹ የተሰጣቸውን ጉሉኮስ እንደነቀሉና ቁስላቸው የተሸፈነበትን ጨርቅ አንስተዋል›› ማለታቸው የተመላከተ ሲሆን፣ ወታደሮቹ የጦር መሳሪያ እንደደቀኑባቸውም ጨምረው ተናግረዋል።

ሆስፒታሉን የሚደግፈው የሕክምና በጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው የድንበር የለሽ ሐኪሞች ቡድን ክስተቱ ማጋጠሙን አረጋግጧል።

የሀኪሞች ቡድኑ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው፣ ወታደሮቹ በሆስፒታሉ ውስጥ በሚገኙ ክፍሎች ውስጥ እየተዘዋወሩ ‹‹አስታማሚዎችንና የጤና ሠራተኞችን አስፈራርተዋል››፡፡ አክሎም ‹‹የሕክምና ተልዕኮዎችን ገለልተኝነት በሚጥስ ሁኔታ በተደጋጋሚ የሚከሰቱት የታጠቁ ቡድኖች ተደጋጋሚ ድርጊት በእጅጉ ያሰስበናል›› ሲልም በመግለጫው ላይ አመልክቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img