Sunday, November 24, 2024
spot_img

በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ 46 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 11፣ 2013 ― በአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት 1 ሰአት ከ30 ገደማ 61 ሰዎችን ጭኖ ወደ ባሕር ዳር ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከቅጥቅጥ አይሱዙ ጋር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ተጋጭቶ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 46 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበበ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ እንደገለጹት፣ በትራፊክ አደጋው ሁለቱም ተሽከርካሪዎች ተገልብጠው 46 ሰዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር እስካሁን ምንም የሞተ ሰው የለም፡፡

በትራፊክ አደጋው የተጎዱ ሰዎች ወደ አቤት ሆስፒታልና ሌሎች የሕክምና ማዕከላት መወሰዳቸውንም ነው ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ገልጸዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ፣ የተገለበጡ ተሽከርካሪዎች በክሬን ተነስተው መንገዱ ለትራፊክ ክፍት መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

በሁሉም ቦታዎች እየደረሱ ያሉት የትራፊክ አደጋዎች መንስኤ ደንብ መተላለፍ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በተለይም ለማሽከርከር አስቸጋሪ በሆኑ መንገዶች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

የሱሉልታ መንገድ ዳገታማ፣ ጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በመሆኑ አሸከርካሪዎች ይህን ተረድተው ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

ሥፍራው ከዚህ በፊትም በተለያዩ ጊዜያት በርካታ አደጋዎች ሲያስተናግድ የነበረ አካባቢ እንደነበር ጠቁመው፥ በማንኛውም ቦታዎች አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው መናገራቸውን የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img