Sunday, October 6, 2024
spot_img

ፍርድ ቤት በነጻ ያሰናበታቸው እነ ኮለኔል ገመቹ አያና በፖሊስ በድጋሚ ቢወሰዱም የት እንደሚገኙ እንደማይታወቅ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ግንቦት 11፣ 2013 ― ከትላንት በስትያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነጻ ያሰናበታቸው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኮለኔል ገመቹ አያና እና ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች ከእስር እንዲወጡ ከተደረገ በኃላ በር ላይ የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱና በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ የፀጥታ ኃይሎች ከበባ አድርገው በመኪና ወስደዋቸው ከአካባቢው እንደተሰወሩ ከቤተሰብ መስማታቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል አቶ ቱሊ ባይሳ ለኦኤምኤን እንደተናገሩት ፍርድ ቤት ተመሳሳይ ውሳኔ የሰጣቸው የመዝገቡ ተከሳሾች ዋና ሳጅን እንጉላ፣ አቶ አማኑኤል እጅጉ፣ አቶ ኪሲ ቂጡማ የስም ስህተት ስላለ በሚል ሳይለቀቁ በመቅረታቸው የነ ኮሎኔል ገመቹ አያና እጣ ሳደርሳቸው ቀርቷል፡፡

ኮለኔል ገመቹ አያና የሚገኙበት በአቶ ኪሲ ቂጡማ የሚጠራው መዝገብ ላይ የተከሰሱት ግለሰቦች የሽብር ጥቃት አድርሰዋል፣ አስተባብረዋል እና አሰማርተዋል ተብለው ነበር የተከሰሱት።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img