Sunday, September 22, 2024
spot_img

ቢል ጌትስ ከአንዲት የኩባንያው ሠራተኛ ጋር ነበረው የተባለ ፆታዊ ግንኙነት እየተጣራ መሆኑ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ግንቦት 10፣ 2013 ― ከዓለማችን የናጠጡ ቱጃሮች መካከል የሆነው ሚስተር ቢል ጌትስ በማይክሮሶፍት ኩባንያ ትሰራ ከነበረች አንዲት ሴት ጋር ከ20 ዓመታት በፊት ፆታዊ ግንኙነት እንደነበረው በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም ግዙፉ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ቢሊዮነሩ ከሰራተኛዋ ጋር ፆታዊ ግንኙነት ነበረው ተብሎ እየተንሰራፋ ስለሚገኘው ወሬ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የማጣራት ሂደቱ የተጀመረው በሰራተኛዋ ጥቆማ መሰረት መሆኑንም የዘገበው ሬውተርስ፣ ኩባንያው ክስ ላቀረበችው ሰራተኛው ከአንድ የሕግ ተቋም ጋር በመሆን ድጋፍ እያደረገላት እንደሆነም ነው አስነብቧል፡፡

ክሱ እየቀረበ ያለው ቢል ጌትስ ከኩባንያው የቦርድ አባልነት በተገለሉበትና ከባለቤቱ መሊንዳ ጋር ፍቺ በፈጸመበት ማግስት መሆኑ በርካቶችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ምርመራው ከተጠቀሱት ጉዳዮች ጋር ምንም የሚያያዝ ነገር እንደሌለው ነው የኩባንያው ቃል አቀባይ የተናገሩት፡፡

የቢል እና መሊንዳ ለ27 ዓመታት የቆየ ትዳር በቅርቡ በፍቺ መቋጨቱ የሚታወስ ነው፡፡ የ65 ዓመቱ ጌትስ 4ኛው የዓለማችን ቢልየነር ሲሆን፣ 124 ቢልዮን ዶላር የሚገመት ሀብት አለው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img