Sunday, November 24, 2024
spot_img

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሦስት የቻይና ዜጎችን ማገቱን ሐሰት ነው ሲሉ የዞኑ ባለሥልጣን አስተባበሉ

Update: በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ሦስት ቻይናውያን የማዕድን አውጪ ኩባንያ ሠራተኞች በታጣቂዎች ታግተዋል መባሉን ሐሰት ነው ሲሉ የዞኑ ባለሥልጣን አስተባበሉ።

እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራ ቡድን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ አቅራቢያ ሦስት የቻይና ዜጋ የሆኑ የማዕድን ሠራተኞችን አግቼ ይዣለሁ ብሎ ነበር።

ይሁን እንጂ የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ በዞኑ ውስጥ ታግቶ የሚገኝ የውጭ ዜጋ የለም በማለት ቡድኑ ያወጣው መግለጫ ሐሰት ነው እንዳሉት ቢቢሲ ዘግቧል።

አቶ ኤልያስ ጨምረውም “በዞኑ ውስጥ ታግቶ የሚገኝ ቻይናዊ አለመኖሩን አረጋግጫለሁ” ማለታቸውም በዘገባው ተመላክቷል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አግቻለሁ ያላቸው ቻይናዊያን ሥማቸው ሁዋንግ፣ ሂ እና ዋንግ እንደሚባሉ ገልጾ ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img