Saturday, November 23, 2024
spot_img

ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ትዳራቸው መፍረሱን ይፋ አደረጉ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 26፣ 2013 ― ቱጃሮቹ ጥንዶች ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ 27 ዓመታት የዘለቀው ትዳራቸው መፍረሱን በትዊተር ገጻቸው ላይ በጋራ ባሰፈሩት ትዊት አስታውቀዋል፡፡

ጥንዶቹ ባሰፈሩት መልእክት ብዙ አውጥተው አውርደው በመጨረሻ ትዳራቸው እንዲያበቃ ከውሳኔ ላይ እንደደረሱ ነው የገለጹት፡፡

የ65 ዓመቱ ቢል ጌትስ እና የ56 ዓመት እድሜ ያላት ሜሊንዳ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በፈረንጆቹ በ1987 ሜሊንዳ የቢል ጌትስ ማክሮሶፍት ኩባንያን በፕሮዳክት ማናጀርነት በተቀላቀለችበት ወቅት ሲሆን፣ ግንኙነታቸው አድጎ በመሠረቱት ትዳር ሦስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡

‹‹በትዳር ዘመናችን ሦስት አስደናቂ ልጆችን እንዲሁም በመላው ዓለም ያሉ ዜጎች ጤናማ እና ፍሬ ያለው ኑሮ እንዲመሩ ለማስቻል ቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽንን አፍርተናል›› ያሉት ጥንዶቹ፣ በትዳራቸው መቀጠል ባይችሉም የፋውንዴሽኑን ሥራ ግን አብረው እንደሚከውኑ ገልጸዋል፡፡

በ2 ሺሕ የተመሠረተው ጥንዶቹ የሚመሩት የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ፋውንዴሽን በዋነኝነት በኅብረተሰብ ጤና፣ ትምህርት እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚሠራ ነው፡፡

እንደ ፎርብስ መጽሔት ከሆነ ባልየው ቢል ጌትስ በ124 ቢሊዮን ዶላር ሐብት የዓለማችን አራተኛው ሐብታም ሰው ነው፡፡ የዓለማችን ግዙፉ ሶፍትዌር አምራቹ ማይክሮሶፍት አለቃው ቢል ጌትስ፣ በፋውንዴሽኑ የምሠራው የበጎ አድራጎት ላይ ባተኩር ይሻለኛል በማለት ከቦርድ አባልነቱ የለቀቀው ባለፈው ዓመት ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img