Sunday, October 6, 2024
spot_img

ከቡሬ ወደ ነቀምቴ ሲጓዙ በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ሕይወት ተቀጠፈ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሚያዝያ 23፣ 2013 ― ከምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወደ ነቀምቴ በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሲጓዙ በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ በአመሮ ወረዳ በደረሰ ጥቃት የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል፡፡

በኦነግ ሸኔ ደርሷል የተባለው ጥቃት የተፈጸመው ሟቾቹ የነበሩበት 60 ሰዎችን ጭኖ ነበር የተባለው ተሸከርካሪ ዓባይ በረሃን ተሻግሮ ካለፈ በኋላ መሆኑን ሚዲያው ከጥቃቱ ከተረፉ ሰዎች ሰምቻለሁ ብሏል፡፡

የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ፓሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ብርሃኑ የባሳ ጥቃቱ የደረሰው በአመሮ ወረዳ መሆኑን አረጋግጠዋል ነው የተባለው፡፡

ሕይወታቸው ካለፉት ውስጥ የአማራ እና የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች እንደሚገኙበት የተገለጸ ሲሆን፣ በጥቃቱ ቁጥራቸው ያልታወቁ የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ እና ከጥቃቱ የተረፉትን የማፈላለግ ሥራ እየተከናወነ ነው ተብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img