Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሱዳን ታጣቂዎች በምዕራብ ጎንደር ተኩስ ከፍተው የግብርና ባለሀብቶችን ካምፕ ማቃጠላቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሚያዝያ 22፣ 2013 ― ታጣቂዎቹ በምዕራብ ጎንደር ዞን መንዶካ ልዩ ሥሙ እንዲብሎ በተባለ ቦታ ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋት 4 ሰዓት ተኩስ ከፍተው የግብርና ባለሀብቶችን ካምፕ ማቃጠላቸውን ዶይቸ ቨለ የአካባቢው ነዋሪ ነግረውኛል ብሎ ዘግቧል።

ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአካባቢ ሚሊሺያና ሌሎችም የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ የሱዳን ኃይሎች ተመልሰዋል ሲሉ ነዋሪው ገልጸዋል።

የመተማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፋንታሁን ኪሮስ በበኩላቸው “መከላከያም፣ ፀረ ሽምቅም፣ ሚሊሺያም ወደ ቦታው ልከናል፤ አሁን ተረጋግቷል” እንዳሉት የዜና ወኪሉ በዘገባው አመልክቷል።

መንዶካ ከሱዳን ድንበር 70 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img