Sunday, October 6, 2024
spot_img

ሰላም ኢትዮጵያ!

እንደምን አደራችሁ? ብዙዎቻችሁ ከኦቲዝም ጋር በተገናኘ በጎ ሥራዋ የምታውቋት ወይዘሮ ዘሚ ዩኑስ በኮሮና ቫይረስ ተይዛ ‹‹በጸሎታችሁ አስቡኝ›› እያለች ትገኛለች፡፡ እንደ ወይዘሮ ዘሚ ዩኑስ ሁሉ በዚህ ሰአት 940 ሰዎች በጤና ተቋማት በጽኑ ሕክምና ክፍል በቫይረሱ ላለመሸነፍ ትግል ላይ ናቸው፡፡

ኮሮና እውነት ነው፡፡ በአገራችን ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 69 ሰዎች በቫይረሱ ሰበብ ላይመለሱ አሸልበዋል፡፡ ብዙዎች የሚወዷቸውን ተነጥቀዋል፡፡

ቫይረሱ የሚያደርሰውን ጉዳት አስቀድመን እንከላከል፡፡ ለራሳችንም ሆነ ለምንወዳቸው ስንል እንጠንቀቅ፡፡ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ ማድረግ አይዘንጉ፡፡ ርቀትዎን ይጠብቁ፡፡ በቸር ያውለን፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img