Friday, November 22, 2024
spot_img

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ከኢዜማ ማብራሪያ መጠየቁን አሳወቀ

[et_pb_section fb_built=”1″ admin_label=”section” _builder_version=”3.22″][et_pb_row admin_label=”row” _builder_version=”3.25″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.25″ custom_padding=”|||” custom_padding__hover=”|||”][et_pb_text admin_label=”Text” _builder_version=”4.9.4″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat” hover_enabled=”0″ text_text_color=”#242E3F” text_font_size=”18px” sticky_enabled=”0″]

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 19፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ‹‹የሃገሪቷ ወቅታዊ የደህንነት ስጋት ትንተና›› የሚል ርእስ አሰናድቶታል በተባለ ሰነድ ላይ ሥሜ ተጠቅሷል ያለው ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በጉዳዩ ላይ አፋጣኝ ማብራሪያ እንዲሰጠው መጠየቁን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

ፓርቲው ከኢዜማ የሚሰጠውን ማብራሪያ መሰረት በማድረግ ‹‹አስፈላጊውን ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ ግብረ መልስ የሚወስድ›› መሆኑንም ጨምሮ ገልጧል፡፡

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ኢዜማ ማብራሪያ ይስጥበት ባለው ሰነድ ላይ ለአገሪቱ የደህንነት ስጋት ነው ያለውን ‹‹ጽንፈኝነት›› በቅርብ ጊዜ ወደ ፖለቲካው መድረክ የመጡት ነጻነት እና እኩልነት እንዲሁም እናት የተባሉ ፓርቲዎች የሃይማኖት ጽንፈኝነትን ፖለቲካዊ ቅርጽ እንዲይዝ የማድረግ አቅም አላቸው ብሎ ነበር፡፡

ኢዜማ ፓርቲዎቹን በዚህ ለመፈረጁ ‹‹መሠረታቸው እምነት ተኮር›› መሆኑን በምክንያትነት አስቀምጧል፡፡ በሰነዱ ላይ ከነእፓ ጋር ባንድነት የተጠቀሰው እናት ፓርቲ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር ስለመኖሩ ይህን ዘገባ እስከተተናዳበት ሰአት ድረስ የተሰማ ነገር የለም፡፡

[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]
ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img