Friday, November 22, 2024
spot_img

ከሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ ጋር በተገናኘ ምርጫ ቦርድ የሰጠው ውሳኔ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ

[et_pb_section fb_built=”1″ admin_label=”section” _builder_version=”3.22″][et_pb_row admin_label=”row” _builder_version=”3.25″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.25″ custom_padding=”|||” custom_padding__hover=”|||”][et_pb_text admin_label=”Text” _builder_version=”4.9.4″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat” hover_enabled=”0″ text_text_color=”#242E3F” text_font_size=”18px” sticky_enabled=”0″]

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 19፣ 2013 ― የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አባላት ከክልሉ ውጪ ባሉ የብሔሩ ተወላጆች የሚመረጡበት ሂደትን በተመለከተ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈውን ውሳኔ ውድቅ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ማክሰኞ በዋለው ችሎት የጉባኤ አባላቱ የምርጫ ሂደት የሽግግር መንግሥት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልሉ ሕገ መንግሥት በሚያስቀምጡት መሠረት እንዲካሄድ ሲል ወስኗል።ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሰጠው ሁለት ጭብጦችን ከመረመረ በኋላ ነው።

በዚህም ምርጫ ቦርድ ጉዳዩ ‹‹ሕገ መንግስታዊ ትርጓሜ የሚያሻ ነው። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም›› በሚል ያቀረበውን መቃወሚያ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ፤ የመከራከሪያ ጭብጡን ውድቅ አድርጎታል። ቦርዱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ እና የሐረሪ ህገ መንግስትን መርምሮ ያስተላለፈውን ውሳኔ፤ ‹‹ከሐረሪ ክልል ውጪ ያሉ ዜጎች ቢመርጡ የሚደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ያላስረዳ ነው›› በሚል ሳይቀበለው መቅረቱን የዘገበው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገጽ ነው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ውሳኔውን ያስተላለፈው የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ፤ በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የይግባኝ አቤቱታ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። አቤቱታው የቀረበው ‹‹የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አባላት ከክልሉ ውጪ ባሉ የብሄሩ ተወላጆች መመረጥ አይችሉም›› የሚለውን የምርጫ ቦርድን ውሳኔ በመቃወም እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]
ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img