Sunday, November 24, 2024
spot_img

ፍርድ ቤት ላምሮት ከማል ላይ በ3 ወር ቀላል እስራት እንድትቀጣ ወሰነ

  • ተከሳሿ በእስር በማሳለፏ በነጻ ተሰናብታለች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ታኅሣሥ 15፣ 2014 ― ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተገናኘ ክስ ተመስርቶባት እየተከታተለች የቆየችው ላምሮት ከማል በሦስት ወር ቀላል እስራት እንድትቀጣ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳልፎባታል።

ላምሮት ከማል በመጀመሪያ ከተከሰሰችበት ሀጫሉ እንዲገደል የግድያ ቦታ ማመቻቸት ሽብር ወንጀል በቂ ማስረጃ አልቀረበም ተብሎ በዚሁ ፍርድ ቤት በነጻ መሰናበቷ ይታወቃል።

ዓቃቤ ሕግ ነጻ መባሏን በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ መጠየቁን ተከትሎ የይግባኝ ሰሚ ችሎቱ መዝገቡን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት የነጻ ውሳኔን በመሻር ላምሮት ከማል አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በሽጉጥ በተመታበት ጊዜ በቸልተኝነት እርዳታ ባለመስጠት በወንጀል ህግ አንቀጽ 575 ንዑስ ቁ 1 እንድትከላከል ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

መዝገቡ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት ከተመለሰ በኋላም እንድትከላከል የተደረገበት አንቀጽ ዋስትና አያስከለክልም ሲል ችሎቱ በ5 ሺሕ ብር ዋስ ከዕስር እንድትፈታ ወስኖ ከእስር ተፈታ ነበር።

ከዚህ በኋላ መከላከያ እንድታቀርብ በተሰጠ ቀጠሮ በጽሕፈት ቤት ቀርባ በጽሑፍ መከላከያ ማስረጃ የለኝም ዓቃቤ ህግ ባሰማው ማስረጃ ይፈረድብኝ ስትል ፍርድ ቤቱን ጠይቃ ነበር።

በዚህ ጥያቄ መሰረት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትናንት በነበረ ቀጠሮ እንድትከላከል በተባለችበት አንቀጽ መከላከል ባለመቻሏ የጥፋተኝነት ፍርድ በመስጠት በይደር ለቅጣት ውሳኔ ቀጠሮ ይዞ ነበር።

በዚህም ፍርድ ቤቱ በዛሬ ቀጠሮ ዓቃቤ ህግ ወንጀሉ በጭካኔ እና በለሊት የተፈጸመ መሆኑን ጠቅሶ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ውድቅ አድርጓል።

ተከሳሿ የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለባትና የልጅ እናት መሆኗን ጠቅሳ ያቀረበችውን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ፍርድ ቤቱ ተቀብሏታል።

ፍርድ ቤት ሦስት ወር እስራት የወሰነ ቢሆንሞ ከቅጣት ውሳኔው በላይ በስር ማሳለፏ ተጠቅሶ በነጻ እንድትሰናበት መደረጉን ከችሎት ጉዳዮች ዘጋቢዋ ታሪክ አዱኛ ገጽ ተመልክተናል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img