Friday, November 29, 2024
spot_img

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ የኢትዮጵያ ኢንሳይት ዘጋቢ ከእስር እንዲለቀቅ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ታኅሣሥ 15፣ 2014 ― ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ ኢትዮጵያ ኢንሳይት የተሰኘ የዜና ድረ ገጽ ሪፖርተር የሆነው ኤርሚያስ ተስፋዬ ከእስር እንዲለቀቅ ጠይቋል።

እንደ ሲፒጄ መረጃ ከሆነ ጋዜጠኛ ኤርሚያስ ተስፋዬ ቡራዩ ከሚገኘው ቢሮው በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው ኅዳር 24፣ 2014 ነው።

ጋዜጠኛው በቡራዩ ከታሠረ በርካታ ቀናት ቢያልፉም አሁንም ድረስ ክስ እንዳልተመሠረተበትና የእስሩ ምክንያትም አለመታወቁ ነው የተገለጸው።

በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት በርካታ ጋዜጠኞች እና የብዙኃን መገናኛ ሠራተኞች መታሰራቸው ይታወቃል። ከታሠሩት መካከል መዐዛ መሐመድ ከሮሃ ቲቪ፣ እያስጴድ ተስፋዬ ከኡቡንቱ እና ታምራት ነገራ ከተራራ ኔትወርክ ይገኙበታል።

ኢትዮጵያ ኢንሳይት በፈረንጆቹ 2018 በቀድሞው የኢትዮጵያ የብሉምበርግ ዘጋቢ ኋላም የኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ አጥኚ ዊሊያም ዴቪሰን የተመሠረተ ነው።

በኢትዮጵያ ጉዳይ በመገናኛ ብዙኃን አስተያየት የሚሰጠው የድረ ገጹ መስራች ዊሊያም ዴቪሰን፣ ከኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በመንግስት ተባሯል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img