Sunday, October 6, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ድርድር እንዲቀጥል እየሠራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

[et_pb_section fb_built=”1″ admin_label=”section” _builder_version=”3.22″][et_pb_row admin_label=”row” _builder_version=”3.25″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.25″ custom_padding=”|||” custom_padding__hover=”|||”][et_pb_text admin_label=”Text” _builder_version=”4.9.4″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat” hover_enabled=”0″ text_font_size=”18px” text_text_color=”#242E3F” sticky_enabled=”0″]

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 19፣ 2013 ― በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገውን የሦስትዮሽ ድርድር በቅርቡ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ ይህነኑ በዛሬው እለት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ወቅት ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር የሆነችው ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ድርድሩ እንዲጀመር ትሰራለች የሚል እምነት እንዳላት የተናገሩት አምባሳደር ዲና፣ ለአፍሪካ ኅብረት ካላት አክብሮት አንፃር ድርድሩ በኅብረቱ እንዲቀጥል አሁንም ፅኑ አቋም እንዳላት አንስተዋል።

የግድቡን ድርድር በሚመለከት ሱዳን እና ግብጽ ጉዳዩን ወደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ወደ አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ለመውሰድ ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ በኢትዮጵያ በኩል ግን ተቀባይነት እንደሌለው በተደጋጋሚ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ቃል አቀባዩ በዛሬው መግለጫቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በሚሲዮኖቹ አማካኝነት በሳምንቱ የተሰሩ ሥራዎችን በመግለጫቸው አንስተዋል።በተለይም የአፍሪካ ሩሲያን የትብብር መድረክ ኢትዮጵያ ለማዘጋጀት ፋላጎት እንዳላት ለሩሲያ መንግስት ገልፃለች ብለዋል።

[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]
ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img