Sunday, October 6, 2024
spot_img

አንቶንዮ ብሊንክን በድጋሚ የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ጠየቁ – አዲሱ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ጄፍሪ ፌልትማን በቀጣይ ቀናት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ

[et_pb_section fb_built=”1″ admin_label=”section” _builder_version=”3.22″][et_pb_row admin_label=”row” _builder_version=”3.25″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat”][et_pb_column type=”4_4″ _builder_version=”3.25″ custom_padding=”|||” custom_padding__hover=”|||”][et_pb_text admin_label=”Text” _builder_version=”4.9.4″ background_size=”initial” background_position=”top_left” background_repeat=”repeat” hover_enabled=”0″ sticky_enabled=”0″]

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 19፣ 2013 ― የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንቶንዮ ብሊንክን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደውለው ከኢትዮጵያ መሬት ይወጣሉ የተባሉ የኤርትራ ወታደሮችን በተመለከተና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ማነጋገራቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አስታውቋል፡፡

ብሊንክን የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ እንደሚወጡ መነገሩን በማስታወስ፣ ይህንኑ በአስቸኳይ በተግባር እንዲያረጋግጡ የጠየቁ ሲሆን፣ እነዚሁ የኤርትራ ወታደሮች ከአማራ ክልል ኃይል ጋር በመሆን በትግራይ ክልል ይፈጸማሉ ያሏቸውን የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት እያባሱት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊው ጨምረውም በመላው ኢትዮጵያ እየተባባሰ መጥቷል ያሉት የሰብአዊ ቀውስ እንዲሁም በትግራይ ክልል ደግሞ ተደቅኗል ያሉት የረሃብ ስጋት እግጉን እንደሚያሳስባቸውም ገልጸዋል፡፡

በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላትም ግጭቱን እንዲያስቆሙ በድጋሚ የጠየቁት አንቶንዮ ብሊንክን፣ አዲሱ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ጄፍሪ ፌልትማን በቀጣይ ቀናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነግረዋቸዋል ነው የተባለው፡፡

[/et_pb_text][/et_pb_column][/et_pb_row][/et_pb_section]

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img