Sunday, September 22, 2024
spot_img

አቶ እስክንድር ነጋ ባለቤቴን እና ልጄን በስልክ ማግኘት አልቻልኩም ሲሉ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 11 2014 ― በእስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንብር አቶ እስክንድር ነጋ ከአገር ውጪ የሚገኙት ባለቤቴን እና ልጄን በስልክ ማግኘት አልቻልኩም ሲሉ በዛሬው እለት ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

በችሎቱ የተገኙት አቶ እስክንድር ነጋ፣ ከዚህ ቀደም ከሀገር ውጪ የሚገኙት ባለቤታቸውን እና ልጃቸውን በሳምንት አንድ ጊዜ በስልክ እንዲያገኟቸው ትእዛዝ መተላለፉን አስታውሰው፣ ሆኖም ትእዛዙ እንዳልተፈጸመ አቤት ብለዋል፡፡

ጉዳያቸውን የሚመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎትም ትእዛዙ ለምን እንዳልተፈጸመ የማረሚያ ቤቱ የእስረኞች ኃላፊ ቀርቦ እንዲያብራራ አዲስ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡

ችሎቱ የአአቶ እስክንድር ነጋ እና የፓርቲ ባልደረቦቻቸውን ጉዳይ ለማየት ለታኅሣሥ 15፣ 2014 ቀጠሮ ይዟል፡፡

የአቶ እስክንድር ነጋ ባለቤት ሰርካለም ፋሲል እና ልጃቸው ናፍቆት እስክንድር በአሜሪካ አገር በስደት እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡

አሁን ለፍርድ ቤት ባለቤቴን እና ልጄን በስልክ ማግኘት አልቻልኩም ያሉት አቶ እስክንድር ነጋ የሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተነሳ ሁከት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ሰኔ 24፣ 2012 ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img