Friday, November 29, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያለ መከሰስ መብት በሚሠጣቸው 11 ኮሚሽነሮች ይመራል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 11 2014 ― በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመራና እንዲያመቻች በመቋቋም ላይ የሚገኘው አገራዊ ምክክር ኮሚሽን 11 ያለ መከሰስ መብት የሚሰጣቸው ኮሚሽነሮች ይመሩታል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከፖለቲካ ወገንተኝነት፣ ከማንኛውም የመንግሥት ወይም ሌላ አካል ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ራሱን የቻለ የሕግ ሰውነት ያለው አካል ሆኖ እንደሚቋቋም የተነገረለት ሲሆን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ታኅሳስ 7፣ 2014 ውይይት አድርጎበታል፡፡

ኮሚሽኑን የሚመሩት ኮሚሽኖች ያለ መከሰስ መብት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካልተነሳ፣ ወይም እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር በኮሚሽነርነት በሚያገለግሉበት ወቅት በወንጀል ያለ መከሰስ መብት ይሰጣቸዋል፡፡

በቅርቡ እንደሚቋቋም ለሚጠበቀው ኮሚሽን ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማኅበራት ኮሚሽነር ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦች ተጠቁመው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የሚሾሙ ስለመሆናቸው ተደንግጓል፡፡

የኮሚሽኑ የሥራ ዘመን ለሦስት ዓመታት ሲሆን፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊራዘም እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img