Friday, November 29, 2024
spot_img

የላሊበላ ከተማ ዳግም በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏ ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 11፣ 2014 ― ከሁለት ሳምንታት በፊት ከአራት ወራት ቆይታ በኋላ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሏ ቢነገርም ዳግም የሕወሓት ኃይሎች ተቆጣጥረዋታል ተብላ የነበረችው የላሊበላ ከተማ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ስር መግቧቷ ተዘግቧል፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ይዞት በወጣው ዘገባ እንዳመለከተው በከተማዋ በትላንትናው እለት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ አብያተ ክርስትያናት ያሉበትን ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡  

በዚህ ጉብኝት ወቅት ከአቶ ደመቀ መኮንን በተጨማሪ የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ ከፍተኛ የጦር ጀነራሎችና ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም መገኘታቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

የላሊበላ ከተማ ቀድሞ በሕወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውላ የነበረችው ባለፈው ዓመት ሐምሌ 29፣ 2013 ነበር፡፡ ኃላም ከአራት ወራት ቆይታ በኋላ ከተማዋን የአገር መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች ኃይሎች ተቆጣጥረዋታል የተባለው ኅዳር 22፣ 2014 ነበር፡፡

አንድ ዓመት በተሻገረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጦርነት የአገር መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች ኃይሎች በሕወሓት ቁጥጥር ስር የነበሩ የአማራ እና አፋር ክልል አካባቢዎችን እያስለቀቁ ቆቦ ከተማ መድረሳቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ባሳለፍነው ቅዳሜ ታኅሣሥ 9፣ 2014 አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img