Thursday, November 28, 2024
spot_img

የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች በሥማችን የሚመጣውን ርዳታ እያገኘን አይደለም ማለታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ታኅሣሥ 9፣ 2014 ― በሰሜን ሸዋ የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች፣ ለእኛ ተብሎ ከዕርዳታ ሰጭዎች የሚመጣውን ድጋፍ በአግባቡ እያገኘን አይደለም እንዳሉት ያስነበበው አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ነው፡፡

እንደ ነዋሪዎቹ ከሆነ በሥማቸው ከሚመጣው የዕርዳታ ቁሳቁስ ሕዝቡ አልወሰደም እንዳይባል ብቻ ተቀናንሶ ይሰጣል እንጂ፣ ዕርዳታው በፍትሐዊነት ለሚገባው አካል እየደረሰ አይደለም፡፡

ነዋሪዎቹ ጥቅምት ላይ ይሰጣል ተብሎ 64 ሺሕ ኩንታል ገደማ የስንዴ ዱቄት ገብቶ የነበረ ቢሆንም፣ ለሕዝቡ ገባ ተብሎ የተነገረው ግን 49 ሺሕ ብቻ ነው ሲሉም ቅሬታ ማቅረባቸው ነው የተመላከተው፡፡

የአጣዬ ከተማ የብልጽግና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ተመስገን አደፍረስ በበኩላቸው የነዋሪዎች ቅሬታ በዚህ ሳምንት የተጀመረውን የእርዳታ ስርጭት አያካትትም ያሉ ሲሆን፣ ከኅዳር ወር በፊት በነበረው ላይ ከሆነ፣ አመራሩ የማህበረሰቡን ጥያቄ በመነሻነት በመያዝና ግምገማ በማካሄድ በቀጣይ የሥርጭት ሥርዓቱ መሻሻል እንዳለበት ተስማምቶ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡

የሚቀርበው ዕርዳታ ካለው ተረጅ ቁጥር አንጻር በጣም ውስን መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ኃላፊው፣ ዕርዳታውም የተሟላ ስለማይሆን፣ ስንዴ ይመጣና ከስንዴ ጋር መቅረብ ያለባቸው ተጓዳኝ ነገሮች ስለማይኖሩ በሥርጭቱ ላይ ችግር መፍጠሩንም ገልጸዋል፡፡

ማኅበረሰቡ ያላግባብ የመጠቀም ፍላጎት አለው ካሉ በኋላ፣ አመራሩም ለተጎጅዎች ከማድረስ ይልቅ ወደ ግል ፍላጎት የማዘንበል ችግር እንደታየበትም አንስተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img