Sunday, September 22, 2024
spot_img

በትግራይ ጦርነት የተፈጸሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጣራ ገለልተኛ መርማሪ ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ጸደቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ታኅሣሥ 8 2014 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ባደረገው ልዩ ስብሰባ በትግራዩ ጦርነት የተፈጸሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጣራ ገለልተኛ መርማሪ ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ በድምጽ ብልጫ ማጽደቁን አስታውቋል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው ዓለም አቀፍ መርማሪ ኮሚሽን ለማቋቋም የወሰነው በ21 የድጋፍ ድምጽ፣ በ15 ተቃውሞ እና በ11 ድምጸ ተዓቅቦ መሆኑንም ገልጧል፡፡

የውሳኔ ሐሳቡን ከተቃወሙት መካከል የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆኑት ኤርትራ እና ሶማሊያን ጨምሮ ቡርኪና ፋሶ፣ ካሜሩን፣ ኮትዲቯር፣ ጋቦን እና ናሚቢያ ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም ቻይና፣ ሩሲያ እና ህንድም የኮሚሽኑን ማቋቋም ጨምሮ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እና በደሎችን የሚያወግዘውን የውሳኔ ሃሳብ ከተቃወሙት መካከል ተገኝተዋል፡፡ በአንጻ ሱዳን በውሳኔ ሐሳቡ ድምጽ ከመስጠት ታቅባለች፡፡

በዚሁ ልዩ ስብሰባ ወቅት የምክር ቤቱ አባል የሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ካውንስሉ ልዩ ስብሰባ መጥራቱን እንደሚቃወሙት በጋራ አስታውቀው የነበረ ሲሆን፣ ቡድኑ ኢትዮጵያን አስመልክተው ለምር ቤቱ አዲስ የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡ አካላት የውሳኔ ሃሳባቸውን እንደገና እንዲያጤኑት በስብሰባው ላይ አስተጋብቷል፡፡

በስብሰባው ላይ እንዲቋቋም እውቅና የተሰጠው በኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጸሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እና በደሎችን የሚመረምረው ዓለም አቀፍ ኮሚሽን ጥቅምት 24፣ 2013 ጀምሮ በሁሉም ወገኖች ተፈጽመዋል የሚባሉ የዓለም አቀፍ ሕጋግት ጥሰቶችን የመመርመር ኃላፊነት ተጥሎበታል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img