Thursday, November 28, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ በኢትዮጵያ ጉዳይ የቀረበውን ሪፖርት አዳመጠ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ታኅሣሥ 8 2014 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ በኢትዮጵያ ጉዳይ የቀረበውን ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል፡፡

በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ሪፖርት ያቀረቡት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክትል ኃላፊ ናዳ አል ነሺፍ የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያ በጦርነቱ ሁሉም ተሳታፊ አካላት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የገለጹት ምክትል ኃላፊዋ፣ ሁሉም ተፋላሚ አካላት ወደ ግዛታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዚሁ ሪፖርት ላይ ከተደነገገ አንድ ወር ስላለፈው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከተ ያነሱት ናዳ አል ነሺፍ፣ በአዋጁ ሰበብ ዘጠኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባልደረቦችን ጨምሮ ከ5 ሺሕ እስከ 7 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች መታሠራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ኃላፊዋ አክለውም በፌዴራል መንግስት እና የክልል ባለስልጣናት የትግራይ እና ኦሮሞ ተወላጆችን ኢላማ በማድረግ ተፈጽመዋል ባሏቸው የጥላቻ ንግግሮች እና ብጥብጥ የማነሳሳት ተግባራት ማዘናቸውንም ገልጸዋል፡፡

በዛሬው እለት እየተካሄደ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባን በተመለከተ ቀድሞውኑ የፖለቲካ አላማ አለው ያለው መንግስት፣ ምንም ዐይነት ውሳኔ ቢተላለፍ እንደማይቀበለው ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡ ይህንኑ የኢትዮጵያ አቋም የተመድ ምክትል ተወካይ አምባሳደር ማሕሌት ኃይሉ ባሳለፍነው ረቡዕ አስረድተዋል፡፡

የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ ለመምከር የተሰበሰበው የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከምክር ቤቱ አባላት እና ታዛቢዎች የቀረበለትን አስቸኳይ ጥያቄ በመቀበል መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ይህ ስብሰባ እንዲካሄድ አንድም የአፍሪካ አገር ድምጽ አልሰጠም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img