Thursday, November 28, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ 14 ጋዜጠኞች መታሠራቸውን ሲፒጄ አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ታኅሣሥ 7 2014 በኢትዮጵያ ከጥቅምት 23፣ 2014 ጀምሮ በተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ 14 ጋዜጠኞች መታሠራቸውን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ኮሚቲ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ (ሲፒጄ) አሳውቋል፡፡

ከታሰሩት ጋዜጠኞች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከግል መገናኛ ብዙኃን መሆናቸውን የሚያመለክተው የሲፒጄ ሪፖርት፣ ከመንግስታዊዎቹ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የትግርኛ ክፍል እና ከፋና ታሳሪዎች መኖራቸውንም ነው የጠቀሰው፡፡

በኢትዮጵያ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለጸጥታ አከላት የተለጠጠ ስልጣን መስጠቱን ያመለከቱት የሲፒጄ ከሰሐራ በታች ተወካዩ ሙቶኪ ሙሞ፣ አዋጁ ለነጻው ፕሬስ አስፈሪ መልእከት በማስተላለፍ፣ የሞጋች ጋዜጠኝነት አፍ እንዲዘጋ ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡

ተወካዩ አክለውም የታሰሩ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የጠየቁ ሲሆን፣ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነትን ማፈኛ ሰበብ ከማድረግ ይቆጠብ ብለዋል፡፡  

በኢትዮጵያ ባለፉት አስር ቀናት ከታሰሩ ሚዲያ ላይ ከሚሠሩት መካከል እያስጴድ ተስፋዬ ከኡቡንቱ ቲቪ፣ ታምራት ነገራ ከተራራ ኔትወርክ እና መዐዛ መሐመድ ሮሃ ከተሰኘ የበይነ መረብ ሚዲያ ይጠቀሳሉ፡፡

ከታሳሪዎቹ መካከል የተራራ ኔትወርክ መስራቹ ታምራት ነገራ ባለፈው ሳምንት ዐርብ ታኅሣሥ 1፣ 2014 በአዲስ አበባ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ድረስ ቤተሰቦቹ የት እንደሚገኝ ማወቅ አልቻልንም እያሉ ይገኛሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ትላንት ምሽት መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ ታምራት ነገራን እንዲሁም ላለፉት 27 ቀናት ደብዛው ጠፍቷል የተባለው የአሐዱ ራዲዮ አርታኢ ክብሮም ወርቁ ያሉበት ይፋ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img