Saturday, October 12, 2024
spot_img

አሜሪካ በአፋር እና አማራ ክልሎች በሕወሓት ኃይሎች ደርሰዋል የተባሉ የመሠረተ ልማት ውድመቶች አሳስቦኛል አለች

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ታኅሣሥ 4፣ 2014 ― አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል በአፋር እና አማራ ክልሎች በሕወሓት ኃይሎች ደርሰዋል የተባሉ የመሠረተ ልማት ውድመቶች አሳስቦኛል ብላለች፡፡

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ያልተረጋገጠ ያለውና በክልሎቹ በሕወሓት ኃይሎች ደርሷል የተባለው የመሠረተ ልማት ውድመት፣ አረመኔያዊ ድርጊቶችን እና አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶችን የሚያጠቃልል ስለመሆኑ ጠቅሷል፡፡

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አክሎም ሁሉም የታጠቁ አካላት በንጹሐን ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲተዉ ያሳሰበ ሲሆን፣ አጥፊዎቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ እነዚህ ሪፖርቶች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

ግጭቶችን ለማቆም ብቸኛው ላለችው ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ያላትን ድጋፍ በድጋሚ የገለጸችው አሜሪካ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ከመጠየቅ በተጨማሪ ያለ ቅድመ ሁኔታ ድርድሮች እንዲካሄዱ እንዲሁም ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት እንዲካሄድ ብላለች፡፡

ከሰሞኑ የፌዴራል መንግስት ዳግም የአማራ እና አፋር ክልል በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠሩን ተከትሎ ቀድሞ የሕወሓት ኃይሎች ይዘዋቸው በነበሩ ከተሞች በርካታ ውድመት ማድረሳቸውን የሚያመለክቱ ዘገባዎች መውጣት ጀምረዋል፡፡

የሕወሓት ኃይሎች ውድመት አድርሰዋል ከተባሉባቸው አከባቢዎች መካከል በደሴ ከተማ፣ የደሴ ሪፈራል ሆስፒታልን ሙሉ ለሙሉ መዝረፋቸው እና መውሰድ የማይችሉትን ደግሞ ማውደቸው ተነግሯል፡፡

የሕወሓት ኃይሎች በሆስፒታሉ መድሃኒትን ጨምሮ ትላልቅ የህክምና መሳሪያዎችን ዘርፈው መውሰዳቸውን ለመገናኛ ብዙሃን የገለጹት የሆስፒታሉ ጊዜያዊ አስተባባሪ ጌታቸው መታፈሪያ፣ በተለይ በቅርቡ ተመርቆ በሆስፒታሉ ወስጥ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን የኦክስጅን ማምረቻ ሙሉ ለሙሉ መዝረፋቸውን ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ቡድኑ በሆስፒታሉ በቅርቡ ተገዝተው አገልግሎት መስጠት የጀመሩ አልጋዎችን ደግሞ አውድሟቸዋል ብለዋል፡፡

የሕወሓት ኃይሎች አድርሰውታል ለተባለው ውድመት የሰጡት ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img