Thursday, November 28, 2024
spot_img

በአማራ ክልል በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ሥራ ለማስጀመር ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ተባለ

በአማራ ክልል የሕወሓት ኃይሎች አውድመዋቸዋል የተባሉ ከ4 ሺሕ የሚበልጡ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ሥራ ለማስጀመር ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የተገለጸው በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ባለ ውይይት ላይ ነው፡፡

በዚህ ውይይት ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ህወሓት የትምህርት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን መግለጻቸውን ፋና ዘግቧል፡፡

አያይዘውም እነዚህ ትምህርት ቤቶች ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በመገንባትና በመጠገን ሥራ እንዲጀምሩ ለማድረግ መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተናግረዋል ነው የተባለው፡፡

የትምህርት ተቋማትን መልሶ ሥራ ለማስጀመር በሚደረገው ርብርብ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ነው ሚኒስትሩ አመልክተዋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ማተቤ ታፈረ በበኩላቸው፣ የህወሓት ቡድን በወረራ ይዟቸው በቆዩ የክልሉ አካባቢዎች ከ4ሺህ የሚበልጡ የትምህርት ተቋማት በመውደማቸው በመውደማቸው ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዲሁም 116 ሺህ መምህራን ከሥራ ውጭ ሆነዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img