Wednesday, October 9, 2024
spot_img

የሚኒስትሮች ም/ቤት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን ወደ ፓርላማ መራ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ታኅሣሥ 1 2014 የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባወጣው መረጃ እንዳመለከተው፣ መንግስት በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ይሁኝታ አግኝቶ ሲመረጥ ቃል ከገባባቸው አገራዊ ጉዳዮች መካከል ሁሉን አካታች የሆነ አገራዊ ምክክርና ውይይት በማካሄድ አገራዊ መግባባት እና በአገር ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አንዱ መሆኑን አስታውሷል፡፡

በዚሁ መሰረት መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ ምልዓተ ህዝቡ ተቀራራቢና በአገራዊ አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ አካታች አገራዊ ምክክሩን ተግባራዊ ለማድረግ በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን በመግለጽ፣ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ለውሳኔ መቅረቡንም አመልክቷል፡፡

ምክር ቤቱ በቀረበው የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል ነው የተባለው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img