Monday, September 23, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተዓማኒነት የደረጃ አንድ እውቅና ተሰጠው

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ኅዳር 29 2014 ― የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተዓማኒነት የደረጃ አንድ ወይም ‹ኤ› እውቅና የተሰጠው በዓለም አቀፉ የብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ጥምረት ነው፡፡

ጥምረቱ ደረጃውን የሚሠጠው የተባበሩት መንግሥታት ባጸደቀው ‹‹የፓሪስ መርሆዎች›› በተሰኘው መለኪያ መሰረት ነው፡፡

በመላው ዓለም ያሉ 118 ብሔራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማትን በአባልነት ያቀፈው የዓለም አቀፉ የብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ጥምረት፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በፀሐፊነት የሚመራው ስብስብ ነው።

የደረጃ ለውጡን ተከትሎ ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ፣ ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 9፣ 2014 ድረስ የዓለም አቀፉ የብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ጥምረት የእውቅና ገምጋሚ ንኡስ ኮሚቴ ጠንከራ የግምገማ ሒደት ማድረጉን አስታውሶ፣ ይህንኑ ግምገማ በማለፉ ደረጃውን ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ደግሞ ለተቋሙ የማሻሻያ ሥራዎች ብሎም የኮሚሽኑን ኃላፊነት ለመተግበር ባልደረቦቻቸው ‹‹አስቸጋሪ›› ባሉት ሁኔታ ውስጥ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም ‹‹የኮሚሽኑ ደረጃ ወደ ከደረጃ ቢ ወደ ኤ ከፍ ማለቱ ተቋሙ እንደ አንድ ገለልተኛ እና ውጤታማ የሰብአዊ መብት ተቋም ከዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላቱን የሚያረጋግጥ ምስክር ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ክትትል በማድረግ ሪፖርቶችን ሲያወጣ የቆየው ኢሰመኮ፣ በቅርቡ በትግራይ ውስጥ ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ላይ ከመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ተቋም ጋር በመተባበር ምርመራ አድርጎ ሪፖርቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img