Friday, November 22, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ማንነትን መሠረት ያደረገ እስር ተፈጽሟል መባሉ አሳስቦናል ያሉት 6 አገራት መግለጫ አወጡ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ኅዳር 28፣ 2014 ― በኢትዮጵያ በጥቅምት ወር መገባደጃ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ ማንነትን መሠረት ያደረገ እስር ተፈጽሟል መባሉ አሳስቦናል በማለት መግለጫ ያወጡት አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ኔዘርላንድ፣ ዴንማርክ እና አውስትራሊያ ናቸው፡፡

አሜሪካን ጨምሮ ስድስቱ አገራት የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ ኢትዮጵያውያንን ማንነታቸውን መሠረት በማድረግ እስር ፈጽሟል ለመባሉ አስረጂ በማድረግ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጧቸውን ሪፖርቶች ጠቅሰዋል፡፡

ተቋማቱ ባወጧቸው ሪፖርቶች የትግራይ ተወላጆችን ጨምሮ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቀሳውስት፣ አዛውንቶች እና ልጆች ያሏቸው እናቶች መታሠራቸውን እንደሚያመለክቱ ገልጸዋል፡፡

አገራቱ በአስረጂነት የጠቀሱት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጁን ተከትሎ መንግስት በቁጥጥር ስር ያደረጋቸው ሰዎች ሁኔታ ያሳስበኛል ማለቱ አይዘነጋም፡፡

የስድስቱ ሀገራት የጋራ መግለጫ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ግለሰቦች ያለ ክስ እና ፍርድ ቤት ችሎት ኢ ሰብዓዊ በሆነ መልኩ ታስረው እንደሚገኙ የሚያመለክት ሲሆን፣ አገራቱ ድርጊቶቹን ‹‹የዓለም አቀፍ ህግን የጣሱ ሊሆኑ ስለሚችሉ›› መቆም እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

አሜሪካ እና ካናዳን ጨምሮ አገራቱ ባወጡት መግለጫ ማሳረጊያ ላይ ወታደራዊ መፍትሔ የለውም ያሉት ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በበጦርነቱ ተሳትፎ አላቸው የተባሉት የጎረቤት ኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን መሬት ለቀው ይውጡ ብለዋል፡፡   

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img