Thursday, November 28, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ ጉዳይ ፈጻሚ ተፋላሚ አካላት ተገደው ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ እንዲደረግ ጠየቁ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ኅዳር 27፣ 2014 ― በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ ጉዳይ ፈጻሚ ቪኪ ሃድልስተን፣ የኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ አስገዳጅ ውሳኔ እንዲያሳልፍባቸው የጠየቁት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤትን ነው።

በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ውስጥ የሚገኙት የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች ጠብመንጃቸውን አስቀምጠው ወደ ጠረጴዛ እንዲመጡ አስገዳጅ ውሳኔ እንዲያሳልፍባቸው የጠየቁት ቪኪ ሃድልስተን፣ እርምጃው በአገራቸው አሜሪካ ማዕቀብ ብቻ እንዳይወሰን የመንግስታቱን ድርጅት ጨምሮ ሌሎችም እንዲያደርጉት ወትውተዋል።

ጡረተኛዋ የቀድሞ የአሜሪካ ጉዳይ ፈጻሚ ቪኪ ሃድልስተን፣ ከቀናት በፊት ይፋ በተደረገውና በሕወሃት መሪነት በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት በማቋቋም ዙሪያ በመከረ የበይነ መረብ ውይይት ላይ ለሕወሓት ጦር ድጋፍ ሲሰጡ የተደመጡ ናቸው።

ከውጭ አገራት ዲፕሎማቶች መካከል በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማማቶን እና ሌሎችም በተሳተፉበት ውይይት፣ የተካፈሉት ትውልደ ኢትዮጵያዊትዋ ኢኮኖሚስት ዶክተር እሌኒ ገብረመድህን በበርካቶች ውግዘት አስተናግደዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img